Psalms 127

በእግዚአብሔር መታመን

የሰሎሞን መዝሙረ መዓርግ።

1 እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣
ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤
እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣
ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።
2የዕለት ጕርስ ለማግኘት በመጣር፣
ማልዳችሁ መነሣታችሁ፣
አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው፤
እርሱ ለሚወድዳቸው እንቅልፍን ያድላልና።
ወይም ተኝተው ሳሉ ምግብ ያዘጋጅላቸዋል።

3እነሆ፤ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፤
የማሕፀንም ፍሬ ከቸርነቱ የሚገኝ ነው።
4በወጣትነት የተገኙ ወንዶች ልጆች፣
በጦረኛ እጅ እንዳሉ ፍላጾች ናቸው።
5ኰረጆዎቹ በእነዚህ የተሞሉ፣
የተባረከ ሰው ነው፤
ከጠላቶቻቸው ጋር በአደባባይ በሚሟገቱበት ጊዜ፣
አይዋረዱም።
Copyright information for AmhNASV